Welcome to
College የሥራ ዕድል ፈጠራና እና የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ ልየታ አፈፃፀም ግምገማ

የሥራ ዕድል ፈጠራና እና የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ ልየታ አፈፃፀም ግምገማ

28th December, 2024

ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የሥራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎችን እና የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ ልየታ አፈፃፀምን በመገምገም ቀጣይ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ አስቀመጡ።

በመድረኩ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የልማት ትሩፋት የንቅናቄ  የሱፐርቪዥን ስራ እና  የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ቀጣይ በሚተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተጠቃሚዎች ልየታ፣ የደራጃ ፍረጃ እና የ2ኛ ዙር ተጠቃሚዎች ምርቃት ተገምግሞ የቀጣይ ስራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎች አንፃር የአፈፃፀም ሂደቱን ሱፐርቫይዝ የማድረግ ሥራው ከድጋፍ ጋር ተሳስሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ተግባራዊ በሚደረገው የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ለመለየት የምዝገባ ሥራው መጠናቀቁ በመድረኩ በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተመዝጋቢዎችን በደረጃ የመፈረጅ ሥራውን በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ ማስተቸት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

.

Copyright © All rights reserved.