Welcome to
College በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር ተካሄደ።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር ተካሄደ።

05th April, 2025

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር ተካሄደ።
መጋቢት 24/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ15ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት አንዱ አካል የሆነው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች ፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በከተማዋ በሚገኙ ኮሌጆች በስድስት ክላስተር ተካሂዷል።
የክህሎት ውድድሩ ከዚህ ቀደም በኮሌጅ ደረጃ የተካሄደ ሲሆን በውድድሩ የተሻለ ውጤት ያስመወገቡ ሰልጣኞች ናቸው በዛሬው ዕለት በክላስተር ደረጃ በተካሄደው ውድድር የተሳተፉት።
ውድድሩን አስመልክቶ በኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ በየነ በሰጡን መረጃ የክህሎት ውድድሩ በ19 የሙያ አይነቶች በ104 ሰልጣኞች መካከል እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ዕድገት በክህሎት በማዳበር እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የዘርፉን ዕድገት በማሳደግ ሂደት የክህሎት ውድድሩ ሚናው ጉልህ መሆኑንም አቶ ፀጋዬ ጠቁመዋል።
በክላስተር የተካሄደው የክህሎት ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ የውድድሩ አሸናፊዎች በቀጣይ ከተማ ደረጃ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
.

Copyright © All rights reserved.