Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለሀገራዊ ብልፅግና
የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለሀገራዊ ብልፅግና
16th April, 2025
"የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለሀገራዊ ብልፅግና"
በክፍለ ከተማው አስተዳደር የ2017 የፋሲካ በዓል አስመልክቶ ኢግዚብሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሚያዚያ 06 /2017 ዓ.ም
በኮልፌ
ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፋሲካ በአል ምክንያት በማድረግ በአየር ጤና አደባባይ ኤግዚብሽንና ባዛር የተከፈተ ሲሆን በኤግዚብሽኑ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ከ60 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ሆነዋል።
የ2017 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ በአየር ጤና አደባባይ የተከፈተውን ኤግዚቢሽንና ባዛር የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ ፣በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ አማካሪ አቶ ክፍሌ ገብሬ ፣ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ሌሎች የአስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች በጋራ በመሆን በይፋ ከፍተውታል።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር "የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለሀገራዊ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል የተከፈተውን ባዛርና ኤግዚቢሽን ለሸማቹ ማህበረሰብ የተለያዪ የምርት አይነቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በአሉን በተረጋጋ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችል እንደሆነ ይታመናል።
በኤግዝብሽኑ በርካታ የባህል አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማርና የማር ውጤቶች፣ እንጨትና ብረታብረት ውጤቶች፣ የኢንደስትሪ ምርቶች እንዲሁም ለበአል የሚውሉ የተለያዩ ምርቶች ቀርበዋል።
ኤግዚብሽንና ባዛሩ ከሚያዚያ 06 /2017 እስከ ሚያዚያ 11 /2017 ዓ.ም ለተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ማወቅ ተችሏል።
ኤግዚብሽኑም የክፍለ ከተማው የስራና ክህሎት እና ኢንደስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት በጋራ ተዘጋጅቷል።
.