Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ለ3ኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የህይወት ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
ለ3ኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የህይወት ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
03rd May, 2025
ለ3ኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የህይወት ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሶስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የህይወት ክህሎት ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።
ቢሮው
በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚ 11ሺ 574 ወጣቶች በህይወት ክህሎት እና በስራ ማፈላለግ ላይ ያተኮረ የ12 ቀናት ስልጠና መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰብሀዲን ሱልጣን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለትም ከኮልፌ ቀራኒዮ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤቶች በስተቀር ስልጠናቸውን በብቃት ላጠናቀቁ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች የዕውቅና ሰርተፍኬት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ከቆዩበት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተቀብለዋል።
የስልጠናውን መጠናቀቅ ተከትሎ የፊታችን ዓርብ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩና ለስራ ላይ ልምምድ ብቁ የሆኑ 2ሺ 400 ቀጣሪ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የስራ አውደ ርዕይ እንደሚካሄድ አቶ ሰብሀዲን ተናግረዋል።
በስራ አውደ ርዕዩ በስልጠና ሂደቱ ያለፉ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች ቃለ መጠይቅ በማድረግ ብቁ ሆነው የተገኙትን ብቻ ወደ ስድስት ወር የስራ ላይ ልምምድ የመቀላቀል ስራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሆነ በኢንተርቪው ሂደቱ ያላለፉ ወጣቶች መንግስት በሚያመቻቸው መደበኛ የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል።
.