Welcome to
College ለ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳታፊዎች የሽኝት መርሀ ግብር ተካሄደ።

ለ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳታፊዎች የሽኝት መርሀ ግብር ተካሄደ።

02nd May, 2025

ለ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳታፊዎች የሽኝት መርሀ ግብር ተካሄደ።
ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት፣የተግባራዊ የጥናትና ምርምርና የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሰልጣኞች፣አሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች በከተማ አስተዳደሩ አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ በማበረታታት የሽኝት መርሀ ግብር አካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ በ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የሚሳተፉ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጀምሮ እስከ ከተማ በየዘርፉ የተካሄደ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩን የሚወክሉ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ስራዎች ይፋ ተደርገዋል።
በሽኝት መርሀ በመርሀ ግብሩ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መሀመድ ልጋኒ ቢሮው በአራተኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር አዲስ አበባ በሁሉም ዘርፍ ግንባር ቀደም እንድትሆን በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰው የውድድሩ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ አንደኛ በሚል መርህ ውድድሩን በድል ለመወጣት አስፈላጊውን የስነልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ከተማ አቀፍ 15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በየአመቱ በሚካሄድበት ድባብ ስፓርታዊ ውድድሮችን ጨምሮ በፓናል ውይይት፤ቴክኖሎጂ ሳምንትና ፋሽን ሾው በግንቦት ወር የመጨረሻ ሳምንት እንደሚካሄድ አቶ መሀመድ ጨምረው ገልፀዋል።
ለወራት ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጀምሮ እስከ ከተማ በየዘርፉ በተካሄደው ውድድር አዲስ አበባን በመወከል በአሰልጣኝ ዘርፍ በ19 የሙያ አይነቶች በክህሎት ውድድር፤አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በአሰልጣኝ፣በሰልጣኝ እና በኢንተርፕራይዝ የተቀዱ ሶስት ቴክኒዎሎጂዎች በ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ይቀርባሉ።
አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
.

Copyright © All rights reserved.