Welcome to
College የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክህሎት የበቁ ባለሙያዎች በማፍራት ለከተማችን እድገት እና ብልፅግና የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክህሎት የበቁ ባለሙያዎች በማፍራት ለከተማችን እድገት እና ብልፅግና የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

21st June, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክህሎት የበቁ ባለሙያዎች በማፍራት ለከተማችን እድገት እና ብልፅግና የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
ሰኔ 12/2017 ዓ ም
"የሚያስቡ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የዕውቅናና የማጠቃለያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
የዕውቅና እና የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በክህሎት የበቁ ባለሙያዎች በማፍራት ለከተማችን እድገት እና ብልፅግና የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ የተጀመረውን ሪፎርም አጠናክረው በማስቀጠል ለበለጠ ውጤት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
አቶ ጥራቱ አያይዘውም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በርካታ የፈጠራ ሀሳቦች መኖራቸውን በመግለፅ እነዚህ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ተለውጠው የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ንግግር ያደረጉት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ልጋኒ 15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል ከ150 በላይ ቴክኖሎጂዎች የቀረበበት አውደ ርዕይን ጨምሮ የተግባራዊ ምርምር፣ የቴክኒካል ክህሎት፣ የስፖርት እና የፋሽን ሾው ውድድሮች፣ ፓናል ውይይቶች እና ሌሎች የተለያዩ መርሃ-ግብሮች ሲካሄዱ ቆይተው በስኬት መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
በ15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድረው ያሸነፉ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች የተሸለሙ ሲሆን በጠቅላላ ውጤት ተግባረ-ዕድ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ 1ኛ፣ አቃቂ ቃሊቲ 2ኛ፣ ምስራቅ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ 3ኛ ደረጃ በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።
.

Copyright © All rights reserved.