Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ ሱፐርቪዥን ቡድን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀመረ::
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ ሱፐርቪዥን ቡድን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀመረ::
31st May, 2025
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ ሱፐርቪዥን ቡድን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀመረ::
ላፍቶ፣ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ ሱፐርቪዥን ቡድን በንፋስ
ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመገኘት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
ቡድኑ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ ሲሆን በክፍለ ከተማው ባለፉት አስር ወራት የተከናወኑ የስራ እድል ፈጠራ ስራ አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ በክፍለ ከተማና በወረዳዎች ላይ ምልከታ ማካሄድ ጀምሯል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ሱፐርቪዥኑን አስመልክተው ባደረጉት ገለፃ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የተቋም ግንባታ ስራዎች፣ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገና ድጋፋዊ ሰፐርቪዥን መሆኑን አንስተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ዘርፉ በጣም ሰፊ ከመሆኑ ባሻገር እንደ ሀገርም ልዩ ትኩረት የተሰጠውና የዜጎችን ክህሎት በማልማት ተቋማዊ ኢንደስትሪን በማረጋገጥ ረገድ ተደጋግፎና ተባብሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬ በከፍተኛ አመራር የሚደረግ ድጋፍ ለሚሰሩ ተግባራት ትልቅ አቅምን የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው የተሰሩ ስራዎችን በተገቢው ለማሳየትና ክፍተቶችም ካሉ ወስዶ ለማስተካከል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ሱፐርቪዥን ቡድኑ በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 9 በቢሮ እና በመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን፤ ምልከታው በነገው ዕለትም ቀጣይነት እንዳለው ተመላክቷል።
.