Welcome to
College አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የወጣቶችን አስተሳሰብ

አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የወጣቶችን አስተሳሰብ

05th April, 2025

“የምዘና ስርዓትን አጠናክሮ በማስቀጠል ስራን በተገቢው መንገድ ለሰራ እውቅና መስጠትና መሸለም ለቀጣይ ስራ ስንቅ ነዉ!”
አቶ እንዳልካቸው አስራት
የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ
መጋቢት 23/2017 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የየካ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት የ2017 በጀት የ6ወራት ምዘናን መሰረት በማድረግ የእዉቅናና ሽልማት ኘሮግራም አካሄደ።
የክፍለ ከተማዉ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት የ2017 በጀት የ6ወራት ምዘናን መሰረት በማድረግ ደረጃ ላገኙ ወረዳዎች እና ለባለድርሻ አካላት የእዉቅናና ሽልማት ኘሮግራም አካሄዷል።
የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳልካቸዉ አስራት የምዘና ስርዓትን አጠናክሮ በማስቀጠል ስራን በተገቢው መንገድ ለሰራ እውቅና መስጠትና መሸለም ለቀጣይ ስራ ስንቅ መሆኑን ገልፀዉ በቀሪ ወራት ለመስራት የታቀዱ ስራዎችን በመፈፀም ዉጤታማ ስራ መስራት የተሰጠ ሃላፊነትን ከመወጣት ባሻገር እደሚያሸም ተናግረዋል።
በእዉቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓቱ 1ኛ ወረዳ 9፣ 2ኛ ወረዳ 12፣ 3ኛ ደግሞ ወረዳ 10 ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ደረጃ 4 እ 5ኛ ለወጡ ወረዳዎች ሁለት ወረዳዎች የሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
.

Copyright © All rights reserved.