Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂዱ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂዱ፡፡
01st November, 2024
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ የተመራ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂደ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሪፎርም ትግበራው አኳያ የሄደበት እርቀት እጅግ የሚደነቅና ጥሩ ግብዓት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡
በተለይ መደበኛ ሥራውንና የሪፎርም ሥራውን ጎን ለጎን በተቀናጀ መንገድ የተመራበት መንገድ እጅግ አስተማሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሥራና
ክህሎት ሚኒስቴር የሪፎርም ትግበራ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፤ ሚኒሰቴሩ በቅርቡ ተደራጅቶ ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ አዲሱን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያከናወነ የሚገኘው አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ትግበራ ሂደትን ከመጀመሪያው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ድረስ የተከናወኑ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በሪፎርም ሥራው የተከናወኑ እና የተጠናቀቁ ሥራዎችም የኮሚቴ አባላቱ ተዘዋውረው ተጎብኝተዋል፡፡
ጥቅምት 21፤ 2017
.