Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ።

26th April, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ።
ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የሰራተኞች የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማ እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ግንዛቤ ከተፈጠረላቸው ለ1ሚሊየን 726ሺ 406 ዜጎች 321ሺ 239 የሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 259ሺ 710 የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ከተፈጠሩ የስራ ዕድሎች ውስጥ 9ሺ354 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል።
ዘመናዊ የአሰራር ቴክኖዎሎጂዎችን በመጠቀም ሂደት በዘጠኝ ወራቱ በE-LMIS (በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ) 29ሺ 686 ኢንተርፕራይዞችን ለመመዝገብ ታቅዶ 16ሺ 101 ኢንተርፕራይዞችን መመዝገባቸው በሪፓርቱ ተመላክቷል።
በዘጠኝ ወራቱ 167 ቴክኖሎዎሎጂዎችን ለመቅዳት ታቅዶ ከዕቅድ በላይ181 ቴክኖሎጂዎች የተቀዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 102 ቴክኖሎጂዎች ማሸጋገር መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል።
ቢሮው በዘጠኝ ወራቱ 50 የሰራተኛ ማህበራት ለማደራጀት አቅዶ 47 የሰራተኛ ማህበራት ማደራጀት መቻሉን እና 73 የስራ ክርክር ውሳኔዎች እንዲያገኙ አቅዶ 60 የሚሆኑት ዕልባት እንዲያገኙ ተደርጓል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል በተደረገው ጥረት አበረታች ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል።
መላው አመራር እና ባለሙያ ተቀናጅቶ በመስራቱ ለውጤቱ መመዝገብ አውንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል ያሉቱ አቶ ጥራቱ በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜያት ለውጦችን አጠናክሮ በመቀጠልና ከብልሹ አሰራርና መልካም አስተዳደር ችግር የፀዳ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ አመራር እና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ባለፉት ዘጠኝ ወራት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን በመግለፅ ተግባራቱ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሂደት ፋይዳቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ስራዎችን በዘመናዊ አሰራር መደገፍ እንደሚያስፈልግ የተገለፀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሪፎርም ስራ በማጠናከር፤ የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች ውጤት መተንተን እንዲሁም ኢንተርፕራይዞችን በE-LMIS (በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ) መመዝገብ ላይ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
.

Copyright © All rights reserved.