Welcome to
College ቢሮው ያካሄደው የሪፎርም ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቢሮው ያካሄደው የሪፎርም ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ፡፡

21st June, 2025

ቢሮው ያካሄደው የሪፎርም ስራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ፡፡
ሰኔ 13/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ አሰተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት በአዋጅ ቁጥር 84/2016 የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮን በአራት ዘርፎች በማዋቀር ወደ ስራ እንዲገባ አድርጓል፡፡
ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ሪፎርም ከተደረጉ 16 ተቋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ከሪፎርሙ በኋላ ባስመዘገባቸው ለውጦች ዙሪያ የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ድጋፍና ክትትል አካሂዷል፡፡
በድጋፍና ክትትሉ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር፤ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ በማዋል፤በሰራተኞች ምጥጥን እንዲሁም በየደረጃው በተካሄዱ የሪፎርም ስራዎች የተመዘገቡ ለውጦች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ሂደት ከቢሮ እስከ ወረዳ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ባካሄደው ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር መቻሉን የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ስታንዳርድን እያስጠበቁ ከመሄድ አንፃር የቢሮ ሌይአውትና የአለባበስ ፕሮቶኮል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጠና ጥናት መሰረት ስታንዳድ ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሊጠናቀቅ በተቃረበው የ2017 በጀት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሲስተም ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሌላ በኩል ብልሹ አሰራርን በማስቀረት መልካም አስተዳደር በማስፈን ሂደት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ስርአት ላይ ስራ ፈላጊ ዜጎች እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ተነስቷል፡፡
ቢሮው 11 ዋና እና 35 ንዑሳን አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ እና ስራውን ለማገዝ 716 ኮምፒውተሮች መሰራጨቱ ተጠቁሟል፡፡
በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰው ሃብት ስራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር አበረታች መሆኑን የገለጹ ሲሆን የተጀመሩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተጀመረው የሪፎርም ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ክፍት የስራ መደቦችን ለማሟላት የዘጠና ቀን ዕቅድ አካል አድርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.