Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና አሠራራቸውን በማዘመን የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና አሠራራቸውን በማዘመን የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።
24th January, 2025
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና አሠራራቸውን በማዘመን የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጥር 14/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የስድስት ወር አፈፃፀሙን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የቢሮው
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት ከመድረክ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው አሠራራቸውን በማዘመን የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
አቶ ጥራቱ በዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ መልካም ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀው አሰልጣኞችን እና ሰልጣኞችን ብቁ አድርጎ ከማስመዘን አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
አቶ ጥራቱ አያይዘውም ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አንፃር ለኢንተርፕራይዞች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ አዳዲስ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን በብዛት መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና ብልሹ አሰራሮችን በመለየት ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት አመራሩ ቁርጠኛ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።
በመጨረሻም የኮሌጅ ዲኖች የስድስት ወር ዕቅዳቸውን ከልሰው ሠራተኛውን በማወያየትና የአመራር ውህደት በመፍጠር የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መስራት ይጠበቅባቸዋል በማለት አቅጣጫ ሰጥተዋል።
.