Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ቢሮው የ2017 የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም ምዘና አስመልክቶ ለመዛኝ ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጠ።
ቢሮው የ2017 የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም ምዘና አስመልክቶ ለመዛኝ ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጠ።
19th July, 2025
ቢሮው የ2017 የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም ምዘና አስመልክቶ ለመዛኝ ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጠ።
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በቢሮው ዘርፎችና
ዳይሬክቶሬቶች፣በክፍለ ከተማ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የ2017 የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም ምዘና ላይ ለሚሳተፉ የመዛኝ ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጥቷል።
በኦረንቴሽኑ የምዘና ቡድኑ ለቢሮው ተጠሪ በሆኑ ተቋማት በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራት በመፈተሽ በተቀመጠላቸው ክብደት መሰረት ነጥብ እየሰጠ ከመሄድ አንፃር ሊከተላቸው በሚገቡ መመሪያዎች ዙሪያ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በተመሳሳይ በተግባር አፈፃፀሙ ሂደት በበጀት ዓመቱ የተቀመጡ ዕቅዶችን ከማሳካት አንፃር የባለሙያዎች ምዘና እንደሚካሄድም ተመላክቷል።
የምዘና ስራው በጥብቅ ዲሲፕሊን መመራት ይኖርበታል ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከብልሹ አሰራር ነፃ የሆነ የአፈፃፀም ምዘና በማድረግ ተጠሪ ተቋማቱን አፈፃፀማቸውን መነሻ ያደረገ ጀረጃ እየሰጡ መሄድ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በቢሮው እና በተጠሪ ተቋማት እና የሚካሄደው የምዘና ስራ ከቀጣዮቹ ቀናት ጀምሮ እንደሚካሄድም ይጠበቃል።
.