Welcome to
College በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሔደው የክህሎት ውድድር ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኝ፤ አሰልጣኝ እና ኢንተርፕራይዝ ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሔደው የክህሎት ውድድር ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኝ፤ አሰልጣኝ እና ኢንተርፕራይዝ ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ።

08th March, 2025

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሔደው የክህሎት ውድድር ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኝ፤ አሰልጣኝ እና ኢንተርፕራይዝ ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ።
የካቲት 25/ 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሀገር አቀፍ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር እና የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ በ14ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች እንደመነሻ የቀረበ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት ከኮሌጅ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር መደረግ በሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ዘርፉን በማስተዋወቅ ዜጎች በሀገር ምርት የመጠቀም ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ይረዳል የተባለለት የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ዘርፉን ወደ ፊት የማራማድ ዕቅድ አንዱ አካል እንደሆነም ተጠቁሟል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መሀመድ ልጋኒ በየደረጃው የሚካሄደው የክህሎት ውድድር በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሔደው የክህሎት ውድድር ብቁ ሰልጣኝ፤አሰልጣኝ እና ኢንተርፕራይዝ ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ጥራት ያለው ቴክኖሎጂ እና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪ አሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች በየደረጃው በሚካሄዱ ውድድሮች ብቃታቸውን በማረጋገጥ ለዓለም አቀፍ ውድድሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
<<ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች>> በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ የሚካሄደው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በከተማ ደረጃ 58 የማምረቻ፤94የምርት፤7 ሀገር በቀል እና 12 የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች በድምሩ 178 ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡበት ይጠበቃል።
.

Copyright © All rights reserved.