Welcome to
College የንፋስ ስልክ ፓሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኢንተርፕራይዞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

የንፋስ ስልክ ፓሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኢንተርፕራይዞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

08th March, 2025

የንፋስ ስልክ ፓሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኢንተርፕራይዞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
የካቲት 27/2017 ዓ.ም
በውይይቱ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ማዕቀፍ ዙሪያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎች ኮሌጁ በሚያደርገው ድጋፍ እና በሚያጋጥሟቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ጥያቄ አንስተዋል።
በክፍለ ከተማው በተለያዩ የስራ መስኮች ተደራጅተው የሚገኙት ኢንተርፕራይዞች ኮሌጁ የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀው ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት በገበያው ተፈላጊ ቴክኖሎጂ እንዲያስተላልፍላቸው ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል በሼዶች አካባቢ ያሉት የመሰረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍታት ሂደት የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ ኮሌጁ ከማሰልጠን በላይ የኢንተርፕራይዞችን ሁሉን አቀፍ ችግር ለመፍታት ጥናትን መሰረት ያደረገ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን አቶ ባህሩ ሻፊ ኮሌጁ በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን መነሻ በማድረግ ኢንተርፕራይዞች ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በመድረኩ የተገኙ የክፍለ ከተማው ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ተወካዮች በበኩላቸው ውይይቱ ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ከባለድሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል
.

Copyright © All rights reserved.