Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በቢሮው ሥር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ሥራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።
በቢሮው ሥር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ሥራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።
01st March, 2025
በቢሮው ሥር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ሥራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።
የካቲት 18/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የ90 ቀናት የሪፎርም ሥራዎች አፈፃፀም ውይይት መድረክ አካሂዷል።
ከመድረክ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሪፎርም ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ኮሌጆች የሥልጠና እና የሥራ ቦታን ምቹ ከማድረግ ጀምሮ ሰልጣኞችን እና አሰልጣኞችን በምዘና ማብቃትን፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረገን፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስራዎች እና የዞኒግና ዲፈረንሼሽን ተግባራት አፈፃፀም ላይ ትኩረት በማድረግ ውይይት ተካሂዷል።
መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በጥናት ላይ ተመስርተው የሠው ሀይላቸውን በአመለካከት እና በክህሎት በማብቃት የጀመሩትን የሪፎርም ሥራ አጠናክረው ማስቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።
አቶ ጥራቱ አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ምድረ-ግቢን ለሥራ እና ለሥልጠና ምቹ ከማድረግ ባሻገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ በማስገባት አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
.