Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ሥራ የሌላቸው የከተማችን ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ አመራሩ ቀርቦ ሊያወያያቸውና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተገለፀ።
ሥራ የሌላቸው የከተማችን ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ አመራሩ ቀርቦ ሊያወያያቸውና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተገለፀ።
22nd March, 2025
ሥራ የሌላቸው የከተማችን ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ አመራሩ ቀርቦ ሊያወያያቸውና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተገለፀ።
መጋቢት 12/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የቀጣይ አራት ወራት የሥራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ዕቅድ የአስር ቀናት አፈፃፀሙን ከክ/ከተማ አመራሮች ጋር በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በመድረኩ የአራት ወራት የተከለሠ የሥራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ዕቅድ እና የአስር ቀናት አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
በቀጣዮቹ የንቅናቄ ወራት 131ሺ 328 የሚሆኑ የከተማችን ሥራ ፈላጊ ነዋሪዎች ሥልጠና እንዲወስዱ በማድረግ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው በዕቅዱ ተመላክቷል።
መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከዳቦ በላይ መሆኑን በመግለጽ በየደረጃው የሚገኝ አመራር ለሥራው ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥቶ በኃላፊነት መንፈስ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
እንደ አቶ ጥራቱ ገለፃ በቀጣዮቹ የንቅናቄ ወራት ከብሎክ ጀምሮ ከወላጆች፣ ከሥራ ፈላጊ ወጣቶች እንዲሁም ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በሰፊው በመወያየት በተሠሩ ሥራዎች እና ቀጣይ ልንሠራቸው ባቀድናቸው ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት ሊፈጠር ይገባል ብለዋል።
ሥራ የሌላቸው የከተማችን ወጣቶች በአካባቢያቸው የሚገኙ ፀጋዎችን ተጠቅመው የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ አመራሩ ቀርቦ ሊያወያያቸውና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ አቶ ጥራቱ አሳስበዋል።
.