Welcome to
College በሥራ ቦታዎች ስለሚከሰቱ አደጋዎች፤ የጤና ችግሮች እና መንስኤ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የውል ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርአት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ተካሄደ::

በሥራ ቦታዎች ስለሚከሰቱ አደጋዎች፤ የጤና ችግሮች እና መንስኤ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የውል ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርአት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ተካሄደ::

01st February, 2025

በሥራ ቦታዎች ስለሚከሰቱ አደጋዎች፤ የጤና ችግሮች እና መንስኤ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የውል ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርአት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ተካሄደ::
ጥር 19 ፤ ቀን 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በከተማዋ በሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም በሥራ ቦታዎች ስለሚከሰቱ አደጋዎች፤ የጤና ችግሮች እና መንስኤ ላይ ያተኮረ ጥናት ለማካሄድ የሚያስል የውል ስምምነት ሰነድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ተፈራርሟል።
ጥናቱ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች እንዲሁም የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሥራ ላይ አደጋዎችንና በሥራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን በመከላከል ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ ተናግረዋል።
በአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ጨምሮ ከዚህ ጋር በተያያዘ በድርጅቶች የሚስተዋለውን የምርት መጠን መዋዥቅ እና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ተጠቁሟል።
ጥናቱ በዋናነት በዘርፉ እየገጠመ ያለውን ተግዳሮት በመለየት ድርጅቶች በጥናቱ መነሻነት የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ እና የሰራተኞችን የመደራጀት ምጣኔ በማሻሻል ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።
.

Copyright © All rights reserved.