Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ያካሄደው የሪፎርም ስራ መነሳሳትን የሚፈጥርና የተሻለ ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን የሶማሌ ክልል የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ገለፀ።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ያካሄደው የሪፎርም ስራ መነሳሳትን የሚፈጥርና የተሻለ ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን የሶማሌ ክልል የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ገለፀ።

01st February, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ያካሄደው የሪፎርም ስራ መነሳሳትን የሚፈጥርና የተሻለ ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን የሶማሌ ክልል የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ገለፀ።
ጥር 22/2017 ዓ.ም
በሶማሌ ክልል የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እና በስሩ በሚገኙ ክፍለከተማዎችና ወረዳዎች የሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤቶች እንዲሁም በጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲያካሂድ የቆየውን የሥራ ጉብኝት አጠናቋል።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት እንደ አዲስ ከተደራጀበት ወቅት አንስቶ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ሪፎርሙ የከተማዋን ዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ በሀገሪቱ በሚገኙ አቻ የዘርፉ መዋቅሮች ተምሳሌት የሚሆን ተግባር በማከናወኑ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በቢሮው እና በስራ በሚገኙ መዋቅሮች የስራ ጉብኝት እና የተሞክሮ ልውውጥ አድርጓል።
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ #አቶ አስፋው ለገሰ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ቢሮው የዘርፉን እሳቤ ትርጉም ባለው መንገድ ወደ ተግባር ተለውጦ የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ እንዲችል በሰራው ስራ አበረታች ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል።
ሪፎርሙ በሁሉም የዘርፉ መዋቅሮች ላይ እንዲተገበር ከማድረግ አንፃር በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሪፎርም መካሄዱን የተናገሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ #ዶ/ር አበራ ብሩ የከተማዋን የመልማት ፀጋ መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክህሎት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ መርዋ አብዱላዚዝ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር ልዑክ ቡድኑ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እና በስሩ በሚገኙ መዋቅሮች በነበረው ቆይታ በክልሉ እየተካሄደ ለሚገኘው የሪፎርም ስራ ትምህርት ሰጥቶ ያለፈ መሆኑን ገልፀዋል።
ልዑኩ ጉብኝት ባካሄደባቸው ተቋማት የዘርፉን እሳቤ በመተግበር ሂደት ምቹ የስራ አካባቢ መፈጠሩን እና በዚህ ሂደት እሳቤውን የሚያሳካ አመራር እና ባለሙያ የተደራጀ ከመሆኑ ባሻገር ወቅቱ በሚፈልገው ዘመናዊ የአሰራር ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን መመልከቱን እና ይህንኑ ተግባር ወደ ክልልሉ ለማስፋት እንደሚሰራ ምክትል ኃላፊዋ ተናግረዋል።
.

Copyright © All rights reserved.