Welcome to
College የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ።

የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ።

14th June, 2025

የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ።
ሰኔ 6/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት በስራ ዕድል ፈጠራና በሌማት ትሩፋት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜ 5/2017 በሚከናወኑ የንቅናቄ ስራዎች ላይ ተወያይቷል።
በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት በስራ ፈላጊነት ከተመዘገቡ 390ሺ560 ዜጎች ውስጥ ለ364ሺ5ዐ ዜጎች ግንዛቤ በመፍጠር 345ሺ322 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
የኢንተርፕራይዞችን ውጤታማነት ከማረጋገጥ አንፃር ከ20ሺ በላይ ኢንተርፕራይዞችን በኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ስርዓት በመመዝገብ 11ሺ895 ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀት መቻሉ ተጠቁሟል።
በሌማት ትሩፋ ስራው ዜጎች የምግብ ፍጆታቸውን በራስ አቅም እንዲችሉ ከማድረግ ባሻገር የስራ ዕድል እንዲፈጥር በማረግ ሂደት ከ22ሺ360 በላይ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተነስቷል።
ባለፉት 11 ወራት በስራ ዕድል ፈጠራና ሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የተናገሩት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ ለዚህም በየደረጃው የሚገኝ አመራር ለስራው ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ነው ብለዋል።
ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ መፍጠር የዚህ ትውልድ አሻራ ሊሆን እንደሚገባ ያስገነዘቡት ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር ከተረጂነት የተላቀቀ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር #አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ከመሄድ አንፃር ስራዎቹ አበረታች ቢሆኑም ከዚህ ቀደም አሁንም ያልተዳሰሱ የስራ ዘርፎችን በመፈተሽ ለዜጎች ተጠቃሚነት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በቀጣዮቹ 90 ቀናትም 90ሺ የስራ ዕድል ለመፍጠር ሀገራዊ ምርትን በማሳደግ የውጭ እርዳታን የሚቀንሱ የከተማ ግብና እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ከተረጂነት የተላቀቀ ምርታማ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት የአደጋ ስጋት የሚቀንሱ ተግባራት የቀጣዮቹ 90 ቀናት የርብርብ ማዕከል መሆን እንደሚገባው አቅጣጫ ተቀምጧል።
በውይይት መድረኩ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፤የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
.

Copyright © All rights reserved.