Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸው የኔትወርክ መሰረተ ልማትና የሲስተም ልማት ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ ገመገመ።
ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸው የኔትወርክ መሰረተ ልማትና የሲስተም ልማት ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ ገመገመ።
22nd February, 2025
ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የጀመራቸው የኔትወርክ መሰረተ ልማትና የሲስተም ልማት ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ ገመገመ።
የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኔትወርክ መሰረተ ልማትና የሲስተም ልማት ትግበራ የደረሰበትን ደረጃ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ ገምግሟል።
በግምገማው ከማዕከል እስከ ወረዳ በኔትዎርክ መሰረተ ልማት እና በሲስተም ልማት ትግበራ ወቅታዊ የቴክኒክ ሁኔታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ቢሮው የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ የአንድ መስኮት አገልግሎትን ጨምሮ የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በመዘርጋት ሂደት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ እና ስብሰባዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ ማካሄድ እንዲቻል በቢሮው ስር የሚገኙ የዘርፉ መዋቅሮችን በቴክኖሎጂ የማስተሳሰር ስራ እንዲሰራ በመድረኩ ተጠይቋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው ቢሮው በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ሲስተም ፍተሻ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ የተጀመረውን ተግባር በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በቴክኒክ ቡድኑ ተለይተው የቀረቡ የትኩረት ነጥቦችን በማዳበር በቀጣይ የሲስተም ፍተሻ ተጠናቆ እና ለዘርፉ አመራርና ባለሙያ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተቀምጧል።
.