Welcome to
College ቢሮው ከኢትዮዽያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።

ቢሮው ከኢትዮዽያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።

15th February, 2025

ቢሮው ከኢትዮዽያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።
የካቲት 7 ቀን ፤ 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከኢትዮዽያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳን #አቶ ካሳሁን ፎሎን ጨምሮ የሰራተኞች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንቶች ተገኝተዋል።
ትኩረቱን ከሰራተኞች መብት እና ጥቅም ከማስከበር አንፃር የተካሄደው ውይይቱ የሰራተኞች ቅነሳ የሚያመጣውን ጫና እና በማህበራት የመደረጃት ምጣኔ ዙሪያ በጥልቀት ተወያይቷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ ቢሮው የኢንዱስትሪ ሰላምን የማረጋገጥ ተልዕኮውን በማሳካት ሂደት ከማህበሩ ጋር በቅርበት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት የዘርፉን ተግዳሮቶች ሊቀርፉ የሚችሉ ጥናቶች እየተካሄዱ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን የዕቅዱ አካል በማድረግ እንደ ከተማ አስተዳደር በአርዓያነት ሊጠቀስ የሚችል ተግባር እንደሚከናወን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳን #አቶ ካሳሁን ፎሎን በበኩላቸው ማህበሩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ከቢሮው ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ቢሮው በቀጣይም የሰራተኛ ማህበራት ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ጋር መሰል የውይይት መድረኮችን እንደሚያካሂድ ተጠቁሟል።

.

Copyright © All rights reserved.