Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
More
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
የየካ ክፍለ ከተማ ስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ያዘጋጀው የገና በዓል ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ
የየካ ክፍለ ከተማ ስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ያዘጋጀው የገና በዓል ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ
03rd January, 2025
የየካ ክፍለ ከተማ ስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ያዘጋጀው የገና በዓል ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ::
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
ፅህፈት ቤቱ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ኢንተርፕራይዞች ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እንዲሸጡ የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ባዛር በይፋ ተከፍቷል፡፡
ኤግዚቪሽኑን ያስጀመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ነዋሪው ምርት እንዲያገኝ ለማስቻል በአላትን ምክንያት በማድረግ ብቻ ሳይሆን በየሳምንቱ በእሁድ ገበያዎች ምርቶችን ሲቀርብ መቆየቱን አንስተው የገና በአልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንም ምርትን፣አገልግሎትን እና ጥበብን በሚያሳድግ መልኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳልካቻው አስራት በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን በማስተዋወቅ የሀገር በቀል ምርትን ለማበረታታት እና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚረዳ ጥራቱን የጠበቀ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን ገልፀው ሁሉም በመገበያየት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ መገናኛ የሚገኝ ሲሆን 56 ኢንተርኘራይዞች እና ከ117 በላይ አንቀሳቃሾች የተሳተፉበት ባዛሩ እስከ ታህሳስ 28 እንደሚቆይ ተገልጿል።
.