Welcome to
College ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተውጣጡ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል እና የገላን ጉራ የተቀናጀ የልማትና መኖርያ መንደርን ጎበኙ።

ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተውጣጡ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል እና የገላን ጉራ የተቀናጀ የልማትና መኖርያ መንደርን ጎበኙ።

31st May, 2025

ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተውጣጡ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል እና የገላን ጉራ የተቀናጀ የልማትና መኖርያ መንደርን ጎበኙ።
ግንቦት 22/2017 ዓ.ም
ከተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተውጣጡ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የገላን ጉራ የተቀናጀ የልማትና መኖርያ መንደርን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የተሰሩ የሰው ተኮር ስራዎች አኩሪ ተግባር እንደሆነ፣ የፕሮጀክቶች ግንባታ እጅግ በአጭር ማጠናቀቅ እንደሚቻል የስራ ባህል ለዉጥ በማድረግ የታየበት፣ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2 ደረጃ ት/ቤቶች፣ የተስፋ ብርሃን መመገበያ አዳራሽና ሌሎች በርካታ የልማቶች ተጎብኝተዋል።
በተጨማሪም የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል የሉዑካን ቡድኑ የጎበኘ ሲሆን የዶሮ ክላስተር፣ የወተት ላም እርባታና የወተትና የወተት ተዋፅኦ ምርት አቅርቦት፣ የከብት ማደለብና የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ተግባራት ተጎብኝቷል።

ማዕከሉ በልማት ምክንያት ለተነሺዎች አርሶ አደርና የአርሶ አደር ቤተሰቦችን በማዕከሉ ታቅፈው እና በ11 ሼዶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሆኑ፣ ከመደበኛው የገበያ ዋጋ ባነሰ ዋጋ የእንሰሳት ምርትና ተዋፅኦ እንደሚያቀርብ ከማዕከሉ አስተባባሪዎች ተመላክቷል።
.

Copyright © All rights reserved.