Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
More
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህት ቤት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የከተማ ግብርና ስራዎችን ጉብኝት አካሄደ፡፡
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህት ቤት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የከተማ ግብርና ስራዎችን ጉብኝት አካሄደ፡፡
26th July, 2025
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህት ቤት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የከተማ ግብርና ስራዎችን ጉብኝት አካሄደ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሐምሌ 17/2017 ዓ ም
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህት ቤት በወረዳ 08 በሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የለሙ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተፋሰስ ስራዎችንና የከተማ ግብርና የጓሮ አትክልት ስራዎችን የወረዳና ክፍለ ከተማው የስራና ክህሎት ፅ/ቤት አመራሮችና ባላሞያዎች በተገኙበት ጉብኝት አካሂዷል፡፡
በጉብኝቱም 168 የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ሰሪ ሃይሎች የተደራጁበት በ1 ሄክታር ላይ ያረፈ ከዚህ ቀደም የቆሻሻ መጣያ የነበረ ቦታነን በማልማት የጥቅል ጎመን፣ቆስጣ፣ሰላጣ፣ድንችና ቀይ ስር አትክልት በማምረት ላይ መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን ያመረቱት ምርት ከተጠቃሚዎች ፍጆታ ባለፈ 67ሺ ብር በሽያጭ ካፒታል ማስቀመጣቸውን እንዲሁም የመቀንጨር አደጋ ለደረሰባቸው ህፃናትን ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቅሷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በተፈጠረላቸው የስራ እድል ከራሳቸው አልፈው ሌሎችን የእየረዱ መሆኑንና የገቢ ምንጭ እያገኙ በመሆኑ ለሌሎች አርዓያ መሆናቸውንና ይህንንም ተሞክሮ ለማጋራት በሰፊው እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በጉብንቱ በወረዳው የተሰራ የአካባቢ ልማት ተፋሰስ አፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተሰራውን የወረዳው ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ተጎብኝተዋል፡፡
.