Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ጽህፈት ቤቱ የጀመረውን የሪፎርም ስራ መሰረት ለመጣል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ጽህፈት ቤቱ የጀመረውን የሪፎርም ስራ መሰረት ለመጣል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
03rd January, 2025
ቢሮው የጀመረውን የሪፎርም ሥራ መሠረት ለማስያዝ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገለፀ።
ታህሳስ 23 ፤ቀን 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረው የሱፐር ቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በዝግጅት እና በተግባር ምዕራፍ በፓርቲ እና በመንግሰት ስራ የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም ፈትሿል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በፓርቲ ስራዎች ከዕቅድ አዘገጃጀትና ከአባላት ምልመላ እና ማብቃት፤ ክህሎት መር የስ ዕድል ፈጠራ ከመፍጠር አንፃር ፤ከኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት ከፀጋ ልየታ እስከ ስራ ስምሪት የካናወናቸው ተግባራት ምን እንደሚመስሉ ከሪፎርም በፊት እና ከሪፎርሙ በኃላ የተመዘገቡ ለውጦችን የተመለከተ ሲሆን ለአሰራር ማነቆ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አንፃር የተከናወኑ ተግባራት በተጨባጭ የተመዘገቡ ለውጦችን በጥልቀት ፈትሿል።
ቢሮው በዝግጅት እና በተግባር ምዕራፍ በመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ያለበት ደረጃ አበረታች መሆኑን የገለፁት የሱፐር ቪዥን ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዲዳ ለውጡ በተለይም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና በክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች በግልፅ ታይቷል ብለዋል።
ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንፃር ቢሮው ያካሄደው ሪፎርም በከፍተኛ ሁኔታ እንዳገዘው የተገለፀ ሲሆን የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን እየፈተሹ መሄድ እና በመንግስት ስራዎች የተመዘገበውን አፈፃፀም በፓርቲ እንዲመዘገብ ማድረግ እንደሚገባ ቡድኑ አሳስቧል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የሱፐር ቪዥን ቡድኑን ግብረ መልስ ቢሮው ተቀብሎ ጥንካሬዎችን ለማላቅ እና ድክመቶችን ለማረም እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ክቡር አቶ ጥራቱ አያይዘውም ቢሮው ሪፎርሙን መሰረት ለማስያዝ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
.