Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
አምስት ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ መጭውን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል።
አምስት ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ መጭውን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል።
26th July, 2025
<<አምስት ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ መጭውን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል።>>~ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
የአምስት ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የኢንሼቲቩን የአፈፃፀም ደረጃ በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
በመድረኩ ኢንሼቲቩ ወደ ተግባር ከገባበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገቡ ለውጦች እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቩን ማሳካት እንደሚገባ የገለፁት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ አመራሩ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተከታታይነት ያለው ግምገማ ማካሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።
ኢንሼቲቩን ከክረምት የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ መጭውን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር እንደሚያስችልም ክቡር አቶ ጥራቱ ጨምረው ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ በበኩላቸው ኢንሼቲቩ በሶፍትዌር ኢንዱስትሪው ያለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት በማሟላት ረገድ የራሱ የሆነ አውንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ አባል ተቋማት ኢንሼቲቩን ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡን ማህበራዊ አውድ በጠበቀ መልኩ በስልጠና እንዲያልፉ በማድረግ ሂደት አስፈላጊውን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ አረጋግጠዋል።
በቀጣይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባሩ ላይ በትኩረት በመስራት እና ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የሪፓርት ስርዓት በመዘርጋት ለዕቅዱ ስኬት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።
.