Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ጎሮ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዘወትር ክትትልና ድጋፍ አደረጉ፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ጎሮ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዘወትር ክትትልና ድጋፍ አደረጉ፡፡
12th July, 2025
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ጎሮ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዘወትር ክትትልና ድጋፍ አደረጉ፡፡
በጉብኝቱ የከተማ አስተዳደሩና የቦሌ ክፍለ ከተማ የፕሮጀክቱ ደጋፊ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ 24/7 በትጋት እየተሠራ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መድረሱ አኩሪ ስኬት መሆኑን አቶ ጥራቱ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡ ቀሪ የፕሮጀክቱን ሥራዎች ለማጠናቀቅ ሁሉም አካላት የሚያደርጉትን የተቀናጀ ርብርብ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አቶ ጥራቱ አሳስበዋል፡፡
በተመሳሳይ ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ጎሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አማካይነት እየተገነባ በሚገኘው ፕሮጀክት ሥራ እየተሳተፉ ለሚገኙ አካላት የእራት ግብዣ ተደረገ፡፡
በእራት ግብዣው ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ኃይሌ እንዲሁም የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች እና የወረዳ 13 አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ ቀን ከሌት በጸሐይና በዝናብ እየሠሩ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚተጉ ሠራተኞችና አጋር አካላትንም አበረታተዋል፡፡
.