Welcome to
College በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተማ አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተማ አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

03rd May, 2025

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተማ አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም
በአዳስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አራተኛው ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂና የክህሎት ውድድር በአዲስ አበባ ደረጃ የቴክኖሎጂ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በውድድሩ በኮሌጅ እና በክላስተር ደረጃ በተካሄደው ውድድር አሸናፊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ናቸው በከተማ ደረጃ በመወዳደር ላይ የሚገኙት።
በቴክኖሎጂ ውድድሩ በከተማዋ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ 31 ቴክኖሎጂዎች ውድድር በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ቶልቻ ተናግረዋል።
ውድድሩ ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ዜጎች የሀገራቸውን ምርት የመጠቀም ባህል በማዳበር በአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ውጤታማ ቴክኖሎጂ እና ቴክኖሎጂስት ለመፍጠር እንደሚያግዝ አቶ ሲሳይ ጨምረው ገልፀዋል።
በከተማ ደረጃ እየተካሄደ ባለው ውድድር ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ እና ከማኑፋክቸሪንግ ምርምር ማዕከል የተውጣጡ ዳኞች ውድድሩን በዳኝነት እየመሩ የሚገኝ ሲሆን በውድድሩ ያሸነፉ ቴክኖሎጂዎች በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የቴክኖሎጂና የክህሎት ውድድር እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
.

Copyright © All rights reserved.