Welcome to
Announcement የዘጠና ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የልመናና ተረጂነት ቅነሳ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ተካሄደ።

የዘጠና ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የልመናና ተረጂነት ቅነሳ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ተካሄደ።

09th August, 2025

የዘጠና ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የልመናና ተረጂነት ቅነሳ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ተካሄደ።
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዘጠና ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የልመናና ተረጂነት ቅነሳ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ተግባራቱ የደረሱበት አሁናዊ ሁኔታ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በዘጠና ቀናቱ ለ90ሺ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በተከናወነው ተግባር አበረታች ውጤት መመዝገብ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለማከናወን ከታቀደው ዕቅድ አንፃር ተግባሩ የ103 % አፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በሌማት ትሩፋት ስራውም የዕቅዱን 100 % መፈፀም መቻሉ የተገለፀ ሲሆን ከተረጅነትና ልመና ቅነሳ ጋር በተያያዘ የተግባሩ አፈፃፀም ደካማ መሆኑ ተነስቷል ።
የውይይት መድረኩን የመሩት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በስራ ዕድል ፈጠራና በሌማት ትሩፋት ስራዎች እንዲሁም የልመናና ተረጂነት ቅነሳ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ሀገራችን በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ከተረጂነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ጥረት ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በየደረጃው የታዩ የአፈፃፀም ጉድለቶችን በማረም የተመዘገቡ ስኬቶች እንዳይቀዛቀዙ መትጋት እንሚገም አቶ አብርሀም ጨምረውም ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ በበኩላቸው በስራ ዕድል ፈጠራ ተግባሩ ስራ ፈላጊ ዜጎችን በብሎክ ከማወያየት ባሻገር በስራ ፈላጊነት በመመዝገብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል።
በዚህ ሂደትም የከተማዋን የስራ ዕድል ፀጋ አሟጦ ከመጠቀም አንፃር ያለውን ውስንነት መቅረፍ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
ወቅቱ ለግብርና ስራዎች ምቹ በመሆኑ በዘርፉ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ በእንስሳት እርባታ ያለውን አፈፃፀም ለማሻሻል እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ የተጀመረውን ተግባር በክላስተር ደረጃ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።

በውይይቱ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤የከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች ተገኝተዋል ።
.

Copyright © All rights reserved.