Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የትንሳኤ በዓል ባዛር በይፋ ተጀመረ።
የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የትንሳኤ በዓል ባዛር በይፋ ተጀመረ።
16th April, 2025
የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የትንሳኤ በዓል ባዛር በይፋ ተጀመረ።
ሚያዚያ 07/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በከተማ ደረጃ 539 ኢንተርፕራይዞች እና 1ሺ 571 የሚሆኑ አንሸሳቃሾች የሚሳተፉበት የትንሳዔ በዓል ባዛር በይፋ አስጀምሯል።
በየካ
ክ/ከተማ የተካሄደውን የባዛር ዓውደ ርዕዩን የከፈቱት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ልጋኒ 539 ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት የባዛር ዓውደ ርዕይ በሁሉም ክ/ከተሞች የተከፈተ መሆኑን ገልፀው ሸማቹ ማህበረሰብ የተለያዩ ምርቶችን በአንድ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል።
አቶ መሀመድ አያይዘውም የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኢንተርፕራይዞች ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና በገበያ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ በስድስት ማዕቀፎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀው ኢንተርፕራይዞች የመንግስትን ድጋፍ ከራሳቸው ጥረት ጋር በማቀናጀት ከአገር ውስጥ አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በርትተው መስራት ይገባቸዋል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ባዛሮቹ ሸማችና አምራችን ከማገናኘት ባሻገር ኢንርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል።
.