Welcome to
College 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በከተማ ደረጃ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

4ኛው ሀገር አቀፍ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በከተማ ደረጃ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

16th April, 2025

4ኛው ሀገር አቀፍ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በከተማ ደረጃ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው 4ኛው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል፣ በተግባረዕድ እና በምስራቅ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች "ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች"በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የክህሎት ውድድሩን ያስጀመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መሀመድ ልጋኒ ቢሮው በኮሌጅ ደረጃ እና በክላስተር ኮሌጅ ደረጃ በ19 የሙያ አይነቶች ሲያወዳድር መቆየቱን ያስታወሱ ሲሆን በዛሬው ዕለትም 76 ሰልጣኞች የሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የክህሎት ውድድር መሆኑን ተናግረዋል።
በየደረጃው ሲካሄዱ የቆዩ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተጣጥሞ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ በክህሎት ያዳበረ ዜጋ ለገበያው ለማቅረብ ያስችላል ሲሉም ተናግረዋል።
አቶ መሀመድ አያይዘውም ውድድሩ የሰልጣኞችን ብቃት በተግባር በመፈተሽ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት በምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል እየተካሄደ ባለው ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ ሰልጣኞች በቀጣይ ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 2 በሚካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ከተማዋን ወክለው እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
.

Copyright © All rights reserved.