Welcome to
College 4ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች መካከል መካሄድ ጀመረ።

4ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች መካከል መካሄድ ጀመረ።

08th March, 2025

4ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች መካከል መካሄድ ጀመረ።
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች ፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በሰልጣኞች ደረጃ መካሄድ ጀምሯል።
የክህሎት ውድድሩን በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ተገኝተው በይፋ ያስጀመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መሀመድ ልጋኒ የክህሎት ውድድሩ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ወደ ተግባር በመለወጥ ሂደት የበቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
በኮሌጆች ሰልጣኞች መካከል የፉክክር መንፈስ በመፍጠር እና ተወዳዳሪነታቸውን በማሳደግ በቀጣይ በክላስተር፤በከተማ፤በሀገር አቀፍ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል።
በዛሬው ዕለት በከተማ ደረጃ መካሄድ በጀመረው የሰልጣኞች የህሎት ውድድር ከ480 በላይ ሰልጣኞች በ19 የሙያ ዘርፎች እንደሚወዳደሩ ተጠቁሟል።
.

Copyright © All rights reserved.