Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ድል ተጎናጽፋለች፡፡
በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ድል ተጎናጽፋለች፡፡
12th July, 2025
በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ድል ተጎናጽፋለች፡፡
የስራና
ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሲካሔድ የቆየው የአፍሪካ የስራ ፈጠራ ፎረም የማጠናቀቂያ መርኃ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
ፎረሙ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትስስርን በማላቅ የግብርና እሴት ሰንሰለት፣ ዲጂታላይዜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ማረጋገጥ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ትስስርን ማላቅ ላይ አተኩሮ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በመድረኩ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማትና ሴክተሮች ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሶስት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ የዕውቅና ሰርተፍኬት ተቀብለዋል።
በዚህም መሰረት
1.ለኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ስኬት ባንክ አንደኛ በመውጣት።
2.ሞዴል የአንድ ማዕከል በማደራጀት
፦ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አንደኛ በመውጣት።
፦ንፋስልክ ወረዳ 14 ሁለተኛ በመውጣት።
፦ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሦስተኛ በመውጣት።
3.በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሸን አገልግሎት ዘርፍ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛ በመውጣት።
4.የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መርጃ ስርዓት E-LMIS ጥቅም ላይ በማዋል የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ከፍተኛ ውጤት በማምጣት 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም አጠናቀዋል፡፡
ፎረሙን የኢትዮጵያ መንግሥት ከአፍሪካ ህብረት፣ ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሴክረቴሪያት እና ከኤትሬድ (AeTrade Group) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ታውቋል፡፡
.