በመንግስት የበጀት ድጋፍ የሚተገበረው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶች የህይወት ክህሎትና የስራ ማፈላለግ ክህሎት ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀመረ።
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
በመንግስት የበጀት ድጋፍ የሚተገበረው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶች የህይወት ክህሎትና የስራ ማፈላለግ ክህሎት ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ በዓለም ባንክ ድጋፍ ሲተገበር የቆየውን ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም በኢትዮጵያ መንግስት የውስጥ አቅም ለመተግበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
በዘሬው ዕለትም በከተማዋ በሚገኙ አስራ አንድ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የህይወት ክህሎትና የስራ ማፈላለግ ክህሎት ስልጠና በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
በስልጠናዉ ዕድሜያቸዉ ከ 18 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 12ኛ ክፍል አጠናቀው ምንም ስራ ያላገኙ፤ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች 12ኛ ክፍል ያላጠናቀቁ፤ ያቋረጡና ከ 12ኛ ክፍል በታች፤ እስከ 10ኛ ክፍል በተመሳሳይ መልኩ ትምህርታቸዉን ለመቀጠል ያልቻሉ የከተማው 3000 ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በስልጠናው የከተማ ግብርና፤ ንግድ ስራ፤ ማኑፋክቸሪንግ፤ ኮንስትራክሽንና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ አተኩሮ የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን ለተከታታይ 12 ቀናት እንደሚከታተሉ እና ከስልጠና በኋላ በመረጡት ሙያ ዘርፎች ከአለማማጅ ድርጅቶች ጋር ለ 6 ወር የስራ ላይ ልምምድ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ስልጠናዉን ሲያጠናቅቁ የስራ ልምድ፤ ሰርትፊኬት እንዲሁም የስራ ልምምድ ባደረጉት ድርጅት ላይ የስራ እድል እንደሚፈጠርላቸው ተጠቁሟል፡፡

.