ለአስተዳደር ሙያ ዘርፍ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ለዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
የስራና ክህሎት ቢሮ የዉጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ለ 15ቱም ኮሌጆች
የአስተዳደር ዘርፍ ባለሙያዎች በዛሬዉ እለት በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደራዊ ጉዳዬች ላይ በተደረገ ክትትልና ድጋፍ ግኝት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር አካሂደዋል፡፡
የመክፈቻ እና ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የተፈሪ መኮንን የዋና ዲን ተወካይ የሆኑት አቶ ደመላሽ ተስፋዬ እንዳሉት ቢሮዉ ለኦዲት፤ ለግዥና ንብረት፤ ፋይናንስ፣ ስነ- ምግባር አንዲሁም ለእቅድና በጀት አጠቃላይ ለ15 ኮሌጆች አስተዳደር ዘርፍ ይህን ስልጠና ማዘጋጀቱ ለባለሙያዎች አቅም ከመፍጠርም ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክርና ያሉባቸዉን የክህሎት ክፍተት በመደጋገፍ ለመፍታት የሚየስችል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ሙያዎች በጋራ በመረዳዳት የመስራት ክህሎት ቢዳብር በተቋሙ ዉስጥ የሚፈጠሩ ችግርች በቀላሉ እንደሚቀረፉ ገልጸዉ እንዲህ አይነት ስልጠና ለባለሙያዎች መዘጋጀቱ የተቋሙ ተልዕኮ እንዲሳካ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚያበረክት ገልጸዉ ላዘጋጁት ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የቢሮ የዉስጥ ኦዲቴር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር የሆኑት ወ/ሮ ዘቢደር ሸዋረጋ በበኩላቸዉ በዉጭ ኦዲት ተብሎ ከሚመጣዉ ግኝት፤ በስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና በሚመጡ ጥቆማዎች መነሻ በማድረግና ከአምስት ኮሌጆች የመንግስትን ሃብት ከማስተዳደር (ከሰዉ ሃብት፤ ከግዥ፤ ንብረት፤ በጀት፤ ጋር ተያይዘዉ መመሪያና አዋጅን ተከትሎ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸዉ ሳምፕል እንደወሰዱና ይህንንም ዉጤት መነሻ በማደረግ አስቀድሞ መከላከልና አቅም መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን መድረክ በጋራ ለማዘጋጀት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡
እንደ ዘቢደር አገላለጽ በግኝቱ ላይ መልካም የሆኑ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ክፍተቶችም እንደታዩ ገልጸዉ እነዚህንና መሰል ክፍተቶችን ለመሙላት ቢሮ ከላይ ሆኖ ለተጠሪ ተቋማት ችግሮች ሲከሰቱ ችግሮች ላይ ከማትኮር አስቀድሞ በግኙቱ መሰረት ያሉባቸዉን ክፍተት እንዲያዩና እንዲስተካክሉ ለማድረግ፤ አንዱ ለአንዱ አቅም እንዲሆኑም ለማስቻል ታስቦ መድረኩ እንደተዘጋጀ አስረድተዋል፡፡
አቶ ቴዎድሮስ አሰጋኸኝ ዉጤት ተኮር ስልጠና ዘርፍ የተቋማት ልማት ባለሙያ ስልጠናዉን በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት ሰልጠናዉ በኮሌጅ ደረጃ አጠቃላይ ከንብረት አስተዳደር ጋር ተያያዘዉ ምን ይመስላል በሚል ሁለቱ ተቋማት የአዲስ አበባ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣንና የቢሮአችን የዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ክትትልና ድጋፍ ስራ መነሻ ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡ ስለዚህ ከንብረት አስተዳደር ጋር ያሉትም ክፍተቶች ግብረ-መልስ ለባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን ይህንን ክፍተት ለመሙላት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ ከክፍተቱ ጋር በቀጥታ የሚገናኙትን ክፍሎች ላይ በማትኮር ግንዛቤ እንዲያገኙ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደተሰጠ ገልጸዋል፡፡
የስልጠናዉ ተሳታፊዎችም ይህንን መሰረት በማድረግ በርካታ ጥያቁዎችን በየኮሌጆቻቸዉ እንደ ክፍተት የሚነሱ ችግሮችን በቅንጅታዊ አሰራር ሊፈቱ እንደሚገባ አቶ ቴድሮስ ገልጸዋል፡፡
አጠቃላይ የአስተዳደር ዘርፎች ላይ ያሉት ችግሮች በደንብ ተፈትሾ ለችግሮች እልባት ለመስጠት ይህ ግብረ መልስ እንደ አንድ ጥሩ መነሻ እንደሆነ አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል፡፡
.