Welcome to
Home የአሰልጣኞች ድልድልና ምደባን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የቴክኒክና ሙያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

የአሰልጣኞች ድልድልና ምደባን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የቴክኒክና ሙያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

24th December, 2025

የአሰልጣኞች ድልድልና ምደባን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የቴክኒክና ሙያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  በተጠሪ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አካባቢያዊ የመልማት ፀጋን መሰረት በማድረግ በተገበረው የዞኒንግና  ዲፈረንሼሽን ስትራቴጂ ትግበራ የአሰልጣኞች ድልድልና ምደባን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የቴክኒክና ሙያ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱን የመሩት በቢሮ ሀላፊ ደረጃ  የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ምደባ እና ድልድሉ  መመሪያን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለፅ ይህም አሰልጣኞች በብቃታቸው በመመደብ የስልጠና ጥራትን አስጠብቋል ብለዋል።

ከማህበራቱ ጋር በተካሄደው ውይይት የምደባ ስራው በመመሪያና ግልፅነትን በተከተለ አካሄድ መካሄዱ የተገለፀ ሲሆን የአሰልጣኞችን ጥቅማ ጥቅም ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

.

Copyright © All rights reserved.