Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
More
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የክፍያ ስርአት በዘመናዊ አሰራር ስርአት ለመደገፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የክፍያ ስርአት በዘመናዊ አሰራር ስርአት ለመደገፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
10th October, 2024
የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች የክፍያ ስርአት በዘመናዊ አሰራር ስርአት ለመደገፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የE-school ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው collage information management system ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመሆን በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።
በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የለማው collage information management system የሰልጣኞች የምዝገባ ስርአትን ጨምሮ የክፍያ ስርአትን አካቶ ይዟል።
በዛሬው ዕለት በሥራና ክህሎት ቢሮ ስር በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተካሄደው የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሰልጣኞች የክፍያ ስርአት በዘመናዊ አሰራር ስርአት በመደገፍ ከE-school ፕሮጀክትጋር ተናቦ እንዲሄድ ያስችላል ተብሏል።
ፕሮጀክቱ በቀጣይ ስራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እንደሚያግዝ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በማዕከል ደረጃ ለማደራጀት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።
.