Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
More
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
<<ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ>>የ2017 በጀት ዓመት የተጠሪ ተቋማት ዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ
<<ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ>>የ2017 በጀት ዓመት የተጠሪ ተቋማት ዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ
04th August, 2025
<<ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ>>የ2017 በጀት ዓመት የተጠሪ ተቋማት ዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ ።
ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ <<ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ>> በሚል ሀሳብ የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት ዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካሂዷል።
መርሀ
ግብሩን በንግግር የከፈቱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ቢሮው የከተማዋን ዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ2016 በጀት ዓመት የሪፎርም ስራዎች መሰረት በመጣል በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀዋል።
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመትም በተጠሪ ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች በማፅናት የተሳካ ስራ መሰራቱ ተገልጿል።
በዚህም ቢሮው ሊያሳካ ካቀዳቸው ግብ ተኮር ተግባራት ውስጥ በላቀ ስኬት በማጠናቀቅ በከተማ አስተዳደሩ ካሉት ተቋማት ውስጥ የአንጓዴ ደረጃ ምድብ ውስጥ በመግባት ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉ ተነስቷል።
በዛሬው ዕለት የተካሄደው ዕውቅናና ሽልማት በቀጣይ ለትልቅ ኃላፊነት መነሳሳትን እንደሚፈጥርም ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል።
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው የKPI እና ቁልፍ ተግባራት ምዘና የማዕከል ዓላማ ፈፃሚ ዘርፎች፣ ዳይሬክተሮች፣ቡድኖች ፤ፈፃሚዎች እና የማዕከል አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ቡድኖች ፤ፈፃሚዎች ፤የፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ኮሌጆች፤የክፍለ ከተማና የወረዳ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤቶች የዋንጫ፣ የዕውቅና ሰርተፍኬት እና የኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚህም መሰረት፦
ከክፍለ ከተሞች
1ኛ.አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት
2ኛ.ቂርቆስና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት
3ኛ.ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት
ከፓሊ ቴክኒክ ማሰልጠኛ ኮሌጆች
1ኛ.አቃቂ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
2ኛ.ጀኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
3ኛ.ንፋስ ስልክና ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች
ከኮሌጆች
1ኛ.ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
2ኛ.ለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
3ኛ.የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
የኢንተርፕርነርሽፕ እና የቴክኒካል ክህሎት የልህቀት ማእከል
ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ ብቸኛ የአረንጓዴ ደረጃ ተሸላሚ
ማዕከል ዓላማ ፈፃሚ ዳይሬክተሮች
1ኛ.የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት
2ኛ.የስራ ስምሪት አገልግሎትና የተቋማት ልማት ዳይሬክቶሬት
3ኛ.የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት
ከማዕከል ዓላማ ፈፃሚ ቡድኖች
1ኛ.ህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ቡድን
2ኛ.የሀገር ውስጥ ስራ ስምሪት ቡድን
3ኛ.የማህ/ስራ/አካ/ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማና የኑሮ ማሻሻያ ቡድን
ከማዕከል አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተሮች
1ኛ.የዕቅድ በጀት ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት
2ኛ.የአ/አ/ስታን/ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት
3ኛ.የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
ከማዕከል አስተዳደር ዘርፍ ቡድን
1ኛ.ግዥ ቡድን
2ኛ.የን/አስ/ጠ/አገ/ቡድን
3ኛ.ክፍያና መዝገብ ቤት ቡድን
.