የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች እየተደረገ ያለውን የሰልጣኞች ቅበላ የቅድመ ዝግጅት ሥዎችን ገምግሟል፡፡በመድረኩ በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የነባር እና አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል እየተደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡የሰልጣኞች ቅበላው ፈጣንና ተለዋዋጭ የሆነውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባ፣ ያለፈውን ጊዜ የሚያካክስ፣ የአሁኑን የሥራ ገበያ ፍላጎት ያማከለ እና የቀጣዩን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ መሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡በበይነ መረብ በተካሄደው የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የዘረፉ ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
.