Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ቃኝቶ ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ቃኝቶ ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
10th October, 2024
ንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንተርፕራይዞች ርክክብ እና የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና ክትትል ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ አዱኛ ካሴ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን በጥናት ከመለየት ባሻገር ግኝቱን መሠረት በማድረግ ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ድጋፍ በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ቃኝቶ ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኮሌጁ እያደረገላቸው ያለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለስራቸው አጋዥ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን አቶ ባህሩ ሻፊ በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የኢንተርፕራይዞችን ውጤታማነት በማሳደግ የሀገር ውስጥ የምርት እድገትን በመጨመር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ያስችላል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር #አቶ ሲሳይ ቶልቻ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ በድጋፍ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ኮሌጁ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ለ578 ነባር እና 108 አዲስ ኢንተርፕራይዞች በመረከብ በአምስቱ የትኩረት ዘርፎች በ56 አሰልጣኞች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ እና 15 ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለማሻጋገር ማቀዱን ከኮሌጁያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
.