Welcome to
Home በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

28th February, 2026

የካቲት 20/2018 ዓ.ም 

በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ዙሪያ  የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

እየተካሄደ ያለዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና በዋናነት በ2017  ዓ.ም በጸደቀው አዲሱ ስትራቴጂ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለክታቸው አካላት  ስትራቴጂዉን በዉል ተረድተዉ ተግባራዊ  እንዲያደርጉ ታስቦ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ።

በቢሮ ሃላፊ ደረጃ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የዉጤት ተኮር ስልጠና  እና የተቋማት አቅም ግንባታ  ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ክብርት ወሮ ዳግማዊት ግርማ ስለ ስልጠናው አላማ እንደገለፁት  የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ  አገራችን የኢንዱስትሪ መር ፖሊስ ተግባራዊ  ለማድረግ እንደ አንዱ ምሶሶ ትልቁን ሚና የሚጫወት እንደመሆኑ ይህን አዲሱን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ በተናጠል ሳይሆን በጋራ ፤ እየተናበቡ በጋራ እንደ ቤተሰብ በመሆን እንዲያሳኩ በተለይ ዋና ተዋናዮች ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ በስትራቴጂው ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግ ነው ብለዋል።

አያይዘውም በህብረተሰቡ ዘንድ  ስለ ዘርፍ ያለው አመለካከት በሚፈለገው ልክ ያልተቀየረ ቢሆንም ብዙ ሰልጣኞች ይህን የተዛባ አመለካከት እየሰበሩ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ስልጠና እያገኙ እንደሆነ ገልጸው ይህን የተዛባ አመለካከት ለመቀየርና ስትራቴጂውን ተግባራዊ ማድረግ ከዋና ተዋናዮች ይጠበቃል ብለዋል። ይህ ስትራቴጂ በሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ለኢንዱስትሪ የበቃ፣ ስራ ወዳድና ስራ ፈጣሪ፡  ዜጎችን በማፍራት ባጠረ ጊዜ  ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚናደርገዉ ጉዞ እንደሚሳካ እምነታቸውን ገልጸዋል ።

የሁሉም ክፍለ ከተሞች ም/ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የ15 ኮሌጆች ዋና እና ምክትል ዲኖች እንዲሁም የቢሮ ዳይሬክተሮች እና የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

.

Copyright © All rights reserved.