Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የስራ ባህልን እና ምርታማነትን የማሳደግ ንቅናቄ በክፍል ከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
የስራ ባህልን እና ምርታማነትን የማሳደግ ንቅናቄ በክፍል ከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
14th December, 2024
የስራ ባህልን እና ምርታማነትን የማሳደግ ንቅናቄ በክፍል ከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
ታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት በ3 ወር ንቅናቄ ሲተገብር የቆየው የስራ ባህልን እና ምርታማነትን ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ የማጠቃለያ መድረክ ስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች ፣ እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላቶች በተገኙበት ተካሂዷል።
በማጠቃለያ መድረኩ በጎ አመለካከትን ከመገንባት እና ስራ የመምረጥ ባህላችንን ከመቀየር አንፃር እንዲሁም በአካባቢያችን ያሉ የስራ ፀጋዎችን መለየትና መጠቀም መቻል ፤ አዳዲስ እሳቤዎችንም ወደ ስራ ለማስገባት አስቻይ የሆነ ግንዛቤን የሚፈጥር ሰነድ ቀርቧል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ ባስተላፉት መልዕክት ለሚ ኩራ በብዙ ፀጋዎች የተሞላች ናት። በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየትና በመጠቀም ከራስ አልፎ ለሀገር ግንባታ ማዋል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በ3 ወር የስራ ባህልን እና ምርታማነትን ማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ በ414 ብሎኮች ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በጥቅሉ ከ24 ሺ 20 በላይ ለሚሆኑ ተሳታፊዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ የተቻለ መሆኑን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ ገልፀዋል።
የንቅናቄ መድረኮቹን ከስራና ክህሎት ፅ/ቤት ጋር ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት እንዲሁም ወጣቶችና ስፓርት ፅ/ቤት በትብብር ያዘጋጁት ሲሆን በማጠቃለያ መድረኩ ከኮሪያ በመጡ ባለሙያዎች የአስተሳሰብ ቀረፃ የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጥቷል።
ምንጭ:-ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
.