Welcome to
Home የሙያ ባለቤት መሆን የራስን ስራ በመፍጠር ሀብት ለማፍራት ወሳኙ መንገድ እንደሆነ ተገለፀ።

የሙያ ባለቤት መሆን የራስን ስራ በመፍጠር ሀብት ለማፍራት ወሳኙ መንገድ እንደሆነ ተገለፀ።

06th November, 2023

ጥቅምት 25 ቀን፣ 2016 ዓ.ም
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከስድስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተውጣጡ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከወሰዱ ተማሪዎች ጋር ተወያይቷል።
በውይይቱ አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲን እና ኮሌጁ ስለሚሰጣቸው የስልጠና አይነቶች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
በውይይቱ በኮሌጁ ሰልጥነው በስራ ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች ተገኝተው ተሞክሯቸውን አካፍሏል። ተሞክራቸውን ያካፈሉ ስራ ፈጣሪዎች የራስን ስራ በመፍጠር ሀብት ማፍራት የሚቻለው የሙያ ባለቤት በመሆን እና ጠንክሮ መስራት ሲቻል መሆኑን ገልፀው ተማሪዎቹ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ ገብተው የሙያ ትምህርት እንዲማሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
ከውይይቱ በኋላ የኮሌጁን ምድረ-ግቢ እና ወርክሾፖች ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ተደርጓል።
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ11 የስልጠና ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
.

Copyright © All rights reserved.