Welcome to
College የቢሮውን አገልግሎት አሠጣጥ በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ተቀመጠ።

የቢሮውን አገልግሎት አሠጣጥ በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ተቀመጠ።

25th October, 2024

የቢሮውን አገልግሎት አሠጣጥ በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ተቀመጠ። ጥቅምት 14/2017 ዓ ም የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመን ተግባራዊ ያደረጋቸውንና ለትግበራ በሂደት ላይ የሚገኙ ቴክኖሎጂዎችን አፈፃፀም ገምግሟል። በቢሮው እየተተገበረ ያሉ የLMIS፣ የE-school፣ የWeb Page እና የሌሎች ሲስተሞቾ አፈፃፀም ጥንካሬዎችና ደካማ ጎኖች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። ውይይቱን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በእነዚህ ሲስተሞች አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ ገልፀው ለምቶ በሂደት ላይ የሚገኘው one window systemን በተመለከተ የትግብራ ዕቅድ በማቀድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ብለዋል። በውይይቱ የአዲስ አበባ ኢኖቬሼንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ እንዲሁም የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
.

Copyright © All rights reserved.