Welcome to
College የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 EOMS የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ማረጋገጫ ይፋዊ የማብሰሪያ ስነ-ስርአት ተካሄደ።

የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 EOMS የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ማረጋገጫ ይፋዊ የማብሰሪያ ስነ-ስርአት ተካሄደ።

01st March, 2025

የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 EOMS የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ማረጋገጫ ይፋዊ የማብሰሪያ ስነ-ስርአት ተካሄደ።
የካቲት 15/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 EOMS የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘቱን ምክንያት በማድረግ ይፋዊ የማብሰሪያ ስነ-ስርአት ተካሂዷል።
በማብሰሪያ ስነ-ስርዓቱ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ #ዶ/ር አበራ ብሩ የትምህርትና ስልጠና ፓሊሲውን ወደ ተግባር በመለወጥ ሂደት ኮሌጁ በዛሬው ዕለት ያገኘው የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ጥራት ያለው ስልጠና እና ምርት በማቅረብ የኮሌጁን ተወዳዳሪ ያሳድጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተኬ ብርሃነ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት የኮሌጁን የማሰልጠን እና የማምረት አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል።
የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ በበኩላቸው የISO ሰርተፍኬት ባለቤትነት የጉዞአችን መጨረሻ አደለም የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
ኮሌጁ ቀጣይ ስራዎቻችን በስታንዳርዱ መሰረት በመስራት በሰልጣኞች እና በማህበረሰቡ ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለዉጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ኮሌጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ሰርተፍኬት ካገኙ የማሰልጠኛ ተቋማት መካከል ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቀጥሎ ሁለተኛው ሲሆን በከተማዋ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ደግሞ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል።
.

Copyright © All rights reserved.