Welcome to
College የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

10th October, 2024

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል። በግምገማ መድረኩ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የተከናወነው ዝርዝር ተግባራት ሪፓረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በዝግጅት ምዕራፉ የተቋማዊ ሪፎርም ስራው አንዱ አካል የሆነው ምቹ የስልጠና አካባቢ መፍጠር እና ዕሳቤዎችን የማስረፅ ስራ በስፋት መሰራቱ ተገልጿል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በዕውቀት እንዲመሩ በየደረጃው ብቃት የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በበጀት ዓመቱ ብልሹ አሰራሮች እንዲስተካከሉ በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት ክቡር አቶ ጥራቱ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች ከብልሹ አሰራር ነፃ የሆነ መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል። በቀጣዮቹ ቀናት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ አመራሮች ምዘና እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ውጤቱን መሰረት ያደረገ የሪፎርም ስራ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
.

Copyright © All rights reserved.