Welcome to
College ቢሮው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ጀምሮ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት

ቢሮው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ጀምሮ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት

08th February, 2025

ቢሮው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ጀምሮ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በመዘርጋት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመን እያከናወናወነው ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ።

ጥር 27/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የአስፈጻሚ አካላት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማ መድረክ አካሂዷል።

ቋሚ  ቢሮ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ያዳመጠ ሲሆን ከአባቱ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ገለፃ ቋሚ ኮሚቴው አስፈፃሚ አካላትን በመቆጣጠርና በመደገፍ ሂደት ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ማድረጉ በተቋማቱ መካከል ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጠናከር በማድረግ ለተሻለ አፈፃፀም መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት አቶሜ አበበ (ዶ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር  ቢሮው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ጀምሮ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በመዘርጋት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመን እያከናወነ ያለው ተግባር የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ዶክተር አቶሜ በንግግራቸው በቴክናክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተጀመረውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በስድስት ወራቱ በተቋማቱ አብዛኛው ግቦች መሳካታቸውንና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር፤ አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

.

Copyright © All rights reserved.