Welcome to AATVETB College
Announcement የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ተከትሎ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ተከትሎ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

15th May, 2026

የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ተከትሎ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

ግንቦት 6/2018 ዓ.ም  አዲስ አበባ

የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪ ኮሌጅ አዲሱን የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ (11ዱን ዘረ-መሎች) መሰረት በማድረግ፣ ተቋሙን የማዘመንና የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ስራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን የተቋሙ የአመራሮች ገለጹ።

ኮሌጁ በተለይ በግልና መንግስት አጋርነት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሰልጣኞች ቁጥር እድገት ተጨባጭ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል።

✍️ የተቋማት ልማት፣ የአቅም ግንባታና የሰው ተኮር ስራዎች አቶ ታከለ ኦላኒ (የተቋማት ልማት እና የአቅም ግንባታ አስተዳደር ምክትል ዲን) እንደገለጹት፣ ኮሌጁ በ2018 የልማት ፀጋንና "ዞኒንግን" ታሳቢ በማድረግ በሰባት ዲፓርትመንቶች ስራውን እያከናወነ ይገኛል።

✍️ የግልና መንግስት አጋርነት (PPP) ውጤት፡
ኮሌጁ ከቢሮ ጋር በመተባበር ባቀረበው የፕሮጀክት ፕሮፖዛል መሰረት፣ በውድድር አሸናፊ የሆኑ የግል ባለሀብቶችን ለይቶ ወደ ስራ አስገብቷል። በዚህም በለዘርና ጋርመንት ዘርፍ የተሰማራ አንድ የግል ባለሀብት ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የኮሌጁን ማሽነሪዎችና ወርክሾፖች በጋራ በማልማት ላይ ይገኛል። ይህም መንግስት ሊያወጣው የነበረውን በጀት ከመቆጠብ ባለፈ፣ ተቋሙን ከባለሀብቱ ጋር በጋራ የማዘመን ስራ ውጤታማ በሆነ ሂደት ላይ መሆኑን ያሳያል።
✍️ የተግባረ-ዕድ ልምድ ልውውጥና የቴክኖሎጂ ሽግግር፡-
የኮሌጁ አሰልጣኞች በአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ (ተግባረ-ዕድ) ያለውን የዘመነ አሰራርና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምድ እንዲቀስሙ ተደርጓል። ይህ የልምድ ልውውጥ አሰልጣኞች በኮሌጃችን የማይገኙትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን  ወደ በተግባረ-ዕድ በመሄድ  በራሳቸው ኮሌጅ ያለውን የአሰራርና የቴክኖሎጂ ክፍተት እንዲለዩና እንዲሞሉ ለማስቻል ታስቦ የተደረገ ነው።

✍️ የአቅም ግንባታና ፕሮጀክቶች፡-
ከ"መርሲ ኮርፕ" (Mercy Corps) ጋር በመተባበር 300 ሴቶችን (50% የአካባቢው ማህበረሰብ እና 50% ተፈናቃዮች) በህይወት ክህሎት ለማሰልጠን ስምምነት ተፈርሟል። በተጨማሪም በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) እየተደረገ ያለውን ዓለም አቀፍ ሽግግር ለመቀላቀል ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር ዝግጅት መጀመሩን ጠቁመዋል።

✍️ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የፈጠራ ስራዎች
አቶ አልዓዛር ተክለማርያም (የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ምክትል ዲን) በበኩላቸው ኮሌጁ ከ580 በላይ ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞችን እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።
✍️ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች፡
በዘንድሮው ዓመት በዞኒንግ መስፈርቱ መሰረት በአውቶሞቲቭ፣ በከተማ ግብርና እና በፈርኒቸር ዘርፎች የኢንተርፕራይዞችን ምርታማነትና ጥራት የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች ተሰርተዋል። በተለይም በ16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት የቀረበችው የኤሌክትሪክ ብስክሌት (Electric Bicycle) ከፍተኛ ፍላጎትና የገበያ ትዕዛዝ በማግኘት ለዜጎች አዲስ የስራ እድል በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ  ገልጸዋል።

✍️ታዳሽ ሃይል (Solar Power):  ኢትዮጵያ ያላትን የ13 ወራት የፀሃይ ፀጋ እንደ አማራጭ የሃይል ምንጭ በመጠቀም፣ ቴክኖሎጂን ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ (Green TVET) ጋር የማገናኘት ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
✍️ የኢንኩቤሽን ማዕከል፡ ማንኛውም የፈጠራ ሀሳብ ያለው ዜጋ በማዕከሉ ገብቶ የማሽነሪና የቴክኒክ ድጋፍ በማግኘት ወደ "ስታርታፕ" እንዲሸጋገር ይደረጋል።
✍️ የአካዳሚክ ስኬትና ዲጂታላይዜሽን
አቶ ረመዳን አብዱራህማን (የሰልጣኝ ልማት እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን) ኮሌጁ አዲሱን ስትራቴጂ በመከተሉ የሰልጣኞች ቁጥር በ100% ማደጉን ገልጸዋል።
✍️የሰልጣኞች ውጤት፡
ባለፈው ዓመት 520 የነበረው መደበኛ ሰልጣኝ ቁጥር ዘንድሮ ወደ 1,066 አድጓል። ኮሌጁ በከተማ ደረጃ በተደረጉ የክህሎት ውድድሮች በዉድ ወርክ ፣ በፋሽን ዲዛይንና በሌዘር ዘርፎች የተሻለ ዉጤት  በማስመዝገብ  ተወዳዳሪነቱን አረጋግጧል።
✍️ስማርት ቦርድ (Smart Board):
ስድስት ዲፓርትመንቶች በስማርት ቦርድ በመደራጀታቸው፣ ሰልጣኞች ስልጠናውን በቪዲዮና ኦዲዮ ሴቭ በማድረግ በፈለጉት ጊዜ መልሰው ማየት እንዲችሉና ከዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲራመዱ ተደርጓል።
ወድ ቤተሰቦቻችን የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ከሆኑት ከአቶ መስፍን ቸሩ ጋር የተደረገዉን ቃለ ምልልስ በቀጣይ ክፍል ይዘን እንደምንቀርብ  ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ 

.

Copyright © All rights reserved.