Welcome to
Announcement "ድልድይ የመገንባት ጥበብ"፤ ጄኔራል ዊንጌት ኮሌጅ ከቻይናው ሻንክሲ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ዓለም አቀፍ ትስስር አጸና።

"ድልድይ የመገንባት ጥበብ"፤ ጄኔራል ዊንጌት ኮሌጅ ከቻይናው ሻንክሲ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ዓለም አቀፍ ትስስር አጸና።

22nd April, 2026

"ድልድይ የመገንባት ጥበብ"፤ ጄኔራል ዊንጌት ኮሌጅ ከቻይናው ሻንክሲ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ዓለም አቀፍ ትስስር አጸና። 


አዲስ አበባ | ሚያዝያ 13/ 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ  የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ከቻይናው ሻንክሲ ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ እና ከቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC) ጋር በመሆን አዲስ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ ከፈቱ። ይህ ትብብር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍን ከዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር የተቀረጸውን የ "አጋርነትና ትብብር" (Partnership & Collaboration) DNA በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ተገልጿል። 

"ስምምነት ሳይሆን ድልድይ እየገነባን ነው" - አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ
በምክትል ካንቲባ ምዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ አጋርነት ሰነድ ከመፈራረም ባለፈ በሁለቱ ሀገራትና ተቋማት መካከል ዕውቀትን፣ ባህልንና ዕድልን የሚያገናኝ "ታላቅ ድልድይ" መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም "ዛሬ ብዕራችንን አንስተን ስንፈርም በወረቀት ላይ ስማችንን ብቻ እየጻፍን አይደለም፤ ይልቁንም የተቋሞቻችንን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየከተብን እንጂ" በማለት የሽርክናውን ጥልቀት አስረድተዋል። 

ቢሮ ኃላፊው አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት፤ የነገው ዓለም የቴክኒክ ብቃት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ግንዛቤና ባህላዊ ተለዋዋጭነት ያላቸውን ባለሙያዎች ይፈልጋል። ይህ ሽርክና የሰልጣኞችን የክህሎት ፍላጎትና አቅርቦት ለማጣጣም (Skill Mismatch) ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ በፋኩልቲ ስልጠና፣ በጋራ የዲግሪ ፕሮግራሞችና በዘመናዊ የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። 

"ዘላቂ አጋርነት እንጂ ጊዜያዊ ፕሮጀክት አይደለም" - አቶ መለስ ይግዛው
የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ መለስ ይግዛው በበኩላቸው፤ ተቋማቸው በታሪክ መዝገብ ላይ ብቻ ሳይሆን በፈጠራና በለውጥ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንደሚከተል ገልጸዋል። "እኛ በኮሌጃችን የምናምነው በአጋርነት እንጂ በፕሮጀክት አይደለም፤ ትብብራችንም ተቋማዊ ሽግግርን የሚያረጋግጥና ዓለም አቀፍ መፍትሔዎችን የሚያመነጭ መሆን አለበት" ሲሉ ተናግረዋል። 

ዲኑ አክለውም፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብሮች ዕውቀት ከመለዋወጥ ባለፈ የሰዎችን አቅም የሚያጎለብቱና ዓለምን የሚቀይሩ አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። 

✍️ የስምምነቱ ዋና ዋና ፋይዳዎች፦
ይህ ስልታዊ ስምምነት የሚከተሉትን ዋና ዋና ግቦች ያሳካል ተብሏል፦ 

✍️ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት፦ ሰልጣኞች በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC) እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ካምፓኒዎች ውስጥ ተፈላጊ እንዲሆኑ ያስችላል። 

✍️ የትምህርት ጥራትና ልህቀት፦ የጋራ የትምህርት ግብአቶችና የአሰልጣኞች ስልጠና የኮሌጁን ደረጃ ወደ ኢንዱስትሪ 5.0 ሽግግር ከፍ ያደርገዋል። 

✍️ ይህ የታሪክና የዘመናዊነት ጥምረት፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ወደ አዲስ ከፍታ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥንና ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆኑ አዲስ የብልጽግና በር የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል። 
.

Copyright © All rights reserved.